Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. November 1, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአማራ ክልል ጎጃም የፓርቲውን ጽሕፈት ቤቶች ለመክፈት የተጓዙት ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራውና የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ አዕምሮ አወቀ እና አቶ ልባዊ አበበ ልዩ ስሟ ደንበጫ በተባለች ከተማ ውስጥ ዛሬ ለሦስት ሰዓታት ታስረው ተፈቱ።

 

ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. ከሰዓት ከ10 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በፖሊስ ታስረው ነበር። ፖሊስ ”አናውቃችሁም፣ አላሳወቃችሁንም” በማለት እንዳሰራቸው ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገልፀዋል።

 

የፓርላማ (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) አባል የሆኑት ሁለቱ የአንድነት ፓርቲ መሥራቾች አቶ አዕምሮ አወቀ እና አቶ ልባዊ አበበ እንዲሁም ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው ማሻውን መፈታታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ