በመቱ ሁለት የአንድነት ፓርቲ አስተባባሪዎች ታሰሩ
Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. October 31, 2008) አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤቶችን ለመክፈት በተንቀሳቀሰባቸው የክፍለ ሀገራት ከተሞች ችግሮች እያጋጠሙት መሆኑ ተገለጸ። በመቱ ከተማ ሁለት አስተባባሪዎች ህዝብን አነሳስታችኋል በሚል መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ።
አንድነት ዓመታዊ በጀቱን ይፋ ካደረገ በኋላ በየክፍለ ሀገራቱ በመዘዋወር እስካሁን አምስት ያህል ጽ/ቤቶችን የከፈተ ሲሆን፣ በመቱ ከተማ ቢሮ ለመክፈት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት አስተባባሪዎች አቶ ጎበዜ ዳምጠው እና አቶ ዳንኤል ወ/ገብርኤል የተባሉ ሰዎች ህዝብን በማነሳሳት በሚል ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል።
ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ዓቃቢ ሕግ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሰባት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለቱ ፍርድ ቤቱ ለሣምንት የጊዜ ቀጠሮ በመስጠት አቶ ጎበዜ እና አቶ ዳንኤል በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ባሌ ውስጥም አንድ አስተባባሪ ታስሮ መለቀቁን ለማረጋገጥ ችለናል።



