የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2013

Merkato, Addis Ababa, Ethiopia

የዋጋ ግሽበት፥ የገንዘብ ለውጥ፣ ያልተጠበቁትና ዱብ ዕዳ የኾኑት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች

ኢዛ (ዓርብ ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 10, 2021)፦ የ2013 ዓ.ም. ለመጠናቀቅ ሰዓታት ቀርተውታል። ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት በቀሩት 2013 ዓ.ም. በአገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ከተከሰቱ ክንውኖች አንኳር የኾኑት የብር ለውጥ እና አንደምታውም ከዓመቱ ኢኮኖሚያዊ ክንውኖች ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በ2013

Ethiopians

ጦርነት፣ ምርጫ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን፣ የውጭ ዲፕሎማሲ በዘንድሮው ዓመት ምን ይመስሉ ነበር?

ኢዛ (ሐሙስ ጳጉሜን ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 9, 2021)፦ የ2013 ዓ.ም. መጠናቀቂያ የመጨረሻ ቀናት ላይ ነን። ኢትዮጵያና ዘንድሮ በታሪክ በእጅጉ የሚታሰቡ ክስተቶች የተስተናገዱበት ነው። በይበልጥ ብርቱ ፈተናዎችን ያስተናገደችበት ዓመት ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጉ ክንውኖች የታዩበት ዓመት ቢኾንም፤ በይበልጥ ግን ተደራራቢ ፈተናዎችዋ ጐልተው የታዩበት ዓመት ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአገር ክህደት የተጠረጠሩ 10 የጦር መኮንኖች በእስር እንዲቀጡ የጦር ፍርድ ቤቱ ወሰነ

በአገር ክህደት ከተፈረደባቸው የጦር መኮንኖች

እስከ 18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. August 26, 2021)፦ በአገርና በአገሪቱ ሠራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም፣ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ጉዳያቸው በደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ጦር ፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩ አሥር የጦር መኮንኖች እስከ 18 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽብርተኛው ሕወሓት ልክ የሌለው ዘረፋና ጥፋት በአማራ ክልል

TPLF (The terrorist group)

ንፋስ መውጫና በሌሎችም አካባቢዎች የሴቶች ቀለበት፣ የጆሮ ወርቅ ሀብልና የመሳሰሉትን ሳይቀር ዘርፈዋል

ሪፖርታዥ

ኢዛ (ረቡዕ ነኀሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. August 25, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት በቅርቡ ይዟቸው የነበሩ የአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት መድረሱ እየተገለጸ ነው። የሽብርተኛው ቡድን በገባባቸው ከተሞች በተለይ የፈጸማቸው ዘረፋዎች ከቤት ቁሳቁስ ጀምሮ እስከ ትላልቅ መሠረተ ልማት ግንባታዎችን ነቅሎ እስከመውሰድ የደረሰ መኾኑን ሰሞኑን በተከታታይ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተክለብርሃን አምባዬ ኮንትራክሽን በብድር ዕዳ የተያዙ አምስት ሕንፃዎች ለጨረታ ቀርበዋል

Tekleberhan Ambaye Construction Plc

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሌላ ከሌሎች የግል ባንኮችም ተበድሯል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. August 23, 2021)፦ ከተለያዩ ባንኮች ቢሊዮኖች የሚገመት ብድር በመውሰድ እና ዕዳዎቹን ባለመክፈል በተደጋጋሚ ስሙ የሚነሳው ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ከአምስት በላይ በማስያዣነት ያቀረባቸው ሕንፃዎች ለጨረታ መቅረባቸውን ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይል ወደ ግንባር ሊንቀሳቀስ ነው

ሙስጠፌ መሐመድ

የክልሎች ልዩ ኃይል በቦታው እየደረሱ ነው

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 16, 2021)፦ አገር ለማፍረስ የመጣውን ኃይል በሕብረት ከመታገል ውጪ አማራጭ የሌለ መኾኑን እና የሕወሓትን የሽብር ቡድን ጥቃት ለመከላከል የሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይል ወደ ግንባር ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑ ተገለጸ። ክልሎች የጸጥታ ኃይሎቻቸውን እየላኩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእነእስክንድር ነጋ ላይ ይመሰክራሉ የተባሉ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሳይቀርቡ ቀሩ

Eskinder Nega

በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠረው በሞት እንዲቀጣ ተጠየቀ

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ ከዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእነእስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ የዓቃቤ ሕግ ምስክር በመኾን ለአምስት ቀናት መሰማት ይጀመራል የተባለው ምስክሮች የመስማት ሒደት ሳይካሔድ ቀረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስተዳደሩ አገር የማዳን ተልዕኮ እንዲሳካ ሕዝቡ ድጋፉን እንዲቀጥል ጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ወጣቶች ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ የሕወሓት ሽብርተኛ ቡድን የጀመረው ጥቃት በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም የገፋው በሕልውናችን ላይ የተጋረጠ አደጋ በመኾኑ፤ ቡድኑ የሚያደርሰውን ጥቃት በመመከት አገር የማዳኑ ተልዕኮ እንዲሳካ ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጐን እንዲቆም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርት ገበያው 39.6 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች አገበያየ

ወንድማገኘሁ ነገራ

258 ሚሊዮን ብር ማትረፉንም ገልጿል

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2013 በጀት ዓመት 614,586 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ምርቶችን በ39.6 (በሠላሳ ዘጠኝ ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር ማገበያየቱን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥት በእርዳታ ስም በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን እንደማይታገስ አስታወቀ

Ambassador Redwan Hussein

በሰብአዊ እርዳታ ስም ለሕወሓት ቡድን መሣሪያ ለማስታጠቅ የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸው ተገለጸ

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 15, 2021)፦ በእርዳታ ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው፤ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን መንግሥት የማይታገስ እና የአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሕፃናትን ለውትድርና እየማገደ መኾኑን እያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ነገሩን በአወንታ መመልከታቸው ፍጹም ተቀባይነት እንደማይኖረው የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ