“የተቆለፈበት ቁልፍ” (መጽሐፍ ግምገማ)
ኩችዬ
ርዕስ፤ የተቆለፈበት ቁልፍ (439 ገጽ)
ደራሲ፤ ምሕረት ደበበ ገ/ጻዲቅ (ዶ/ር)
ሮሆቦት አታሚዎች፤ አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2005
አገር ቤቱ ዳያስፖራ፤ ዳያስፖራው ደግሞ አገር ቤት እየሆነ በመጣበት በዚህ ህልሙም፤ ቅዠቱም፤ ባህሉም፤ ኑሮውም ተወራራሽ በሆነበት ዘመን የሥነ ጥበብ ሰዎች አስጎምዥ የትረካ አውድማ እንደተቸሩ ካወቅኹ ሰንብቻለሁ።
የምሕረት ደበበ ልቦለድ ታሪክ ስድሰት ሺህ ማይል አራርቋቸው በሚኖሩ ያበሻ ሕበረተሰቦች ሁለንተናዊ ባሕርይና ዕጣ-ፈንታ ላይ የተመሠረተ ነው። የደራሲው አንድ እግር አሜሪካ፤ ሌላኛው እግር ደግሞ ኢትዮጵያ መሆን የሁለቱንም ሕብረተሰቦች ውጫዊና ሥነ-ዓዕምሮዋዊ ባሕርይ፤ እንዲሁም የየቤቱን ውሎና ከራሞ በቅርብ ለማስተዋል ዕድል እንደሰጠው ከትርካዎቹ ማስተዋል ይቻላል። ሁለቱም ሕብረተቦች ውስጥ እየተከሰተ ያለው ፈጣንና አንዳንዴም አስፈሪ የሆነ ማኅበራዊ ለውጥ የብዙ ደራሲያንን እንዲሁም በየሙያ ዘርፉ ያሉ ጠቢባንን የሰላ አዕምሮና ብዕር የሚጋብዝ ነውና እንደ ምሕረት ደበበ ያሉ ብዕር ሲያነሱ ደስ ይላል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስሜነህ ታምራት (ስዊድን)


