አነጋጋሪው የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ ምጥን ዳሰሳ (ክፍል ሁለት)
መንግሥቱ አበበ
• የአማራ፣ የትግሬ ወይም የኦሮሞ ስርወ - መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም
• “ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል” ብለው ሀውልት ያቆሙ በድርጊታቸው ማፈር አለባቸው
• በ21ኛው ክፍለ ዘመን የግዕዝ ፊደላትን ጠልተን ላቲን ፍለጋ የሄድንበት ምክንያት
ምንድን ነው?

(ካለፈው የቀጠለ)
ባለፈው ሳምንት “አነጋጋሪው የፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ ምጥን ዳሰሳ” በሚል ርዕስ ደራሲው “የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በማለት ለንባብ ባበቁት አዲስ መጽሐፍ ላይ የተደረገ ምጥን ዳሰሳ ማቅረባችን ይታወቃል። ቀሪውን ክፍል እነሆ፡- (ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ”የኦሮሞና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በሚል ርዕስ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. አሳትመው ያወጡት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ምርምርና ጥናት አዲስ ፈር ቀዳጅ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ውጪ (ከማዳጋስካር፣ ከኢስያ ክፍሎች) ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ የገባ ሲባል የኖረውን አፈ ታሪክ አሳማኝ ናቸው በሚባሉ ማስረጃዎች አስደግፈው ከእውነቱ የራቀ መሆኑን አሳይተዋል። ሁለተኛ አማራ የገዥ መደብ ተብሎ በአማራ ሥርወ መንግሥት ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች የባህል ገጽታዎቹን በኃይል ጭኖባቸዋል የሚለው ውግዘት ምንም ታሪካዊ መሠረት እንደሌለውና እንዲያውም፣ በአግአዚ/ሰሎሞናዊና በዛጉዌ ሥርወ መንግሥታት በንጉሠ ነገሥትና ደረጃ አማሮች የበላይነት ይዘው እንደማያውቁና ይልቁንም በዚህ የሥልጣን ደረጃ አብዛኞቹ ኦሮሞዎች እንደነበሩ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በዘመነ መሳፍንት በባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቱ በኢትዮጵያ ሥልጣን ይቀራመቱ የነበሩት አማሮች ሳይሆኑ፣ በተለይ የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ቁልጭ አድርገው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ አመልክተዋል። ሦስተኛ አማሮች የዘር ምድባቸው ሴማዊ (ሴሜቲክ) ሳይሆን እንደ ኦሮሞ ኩሻዊ መሆኑን፣ ሁለቱም ጎሳዎች (ጎሳ በቋንቋ መወሰኑን አመልክተዋል) የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጥንታዊ አባት ከሆነው ኩሻዊው ኢትዮጵያ ልጅ ከደሽት (ከደሴት) የመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ጂኦግራፊያዊ ወይም መልክዓ ምድራዊ ምንጫቸው ዛሬ ጐጃም እየተባለ የሚጠራው አካባቢ መሆኑን አመልክተዋል። እነዚህ ሁሉ አዳዲስ ታሪካዊ ግኝቶች ናቸው።
ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች” በሚል አዲስ መጽሐፍ አስነብቦናል። በአንድ ጋዜጣ ላይ የዶክተር መረራ ከዩኒቨርሲቲ መሰናበት ያመጣው አንድ በጎ ጎን መሆኑን አንብቤያሁ። እኔም በዚህ እስማማለሁ። ብዙ የሀገራችን ፖለቲካኞች ጋዜጠኛ መቅረፀ ድምፅ ይዞ በሚጠይቃቸው ጥያቄ መልስ ከመስጠት የዘለለ ብዕርና ወረቀት አገናኝተው የሚያምኑበትን የፖለቲካ መስመር እና በግላቸው ያላቸውን ምልከታ ማካፈል ይቸግራቸዋል።
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)


