ተስፋዬ ገብረአብ እና የመከነ ብዕሩ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከቡርቃ ዝምታ እስከ የስደተኛው ማስታወሻ

Yesedetegnaw Mestawesha by Tesfaye Gebreab የስደተኛው ማስታወሻ በተስፋዬ ገብረአብመስፍን አማን (ከሃርለም፣ ኔዘርላንድ)

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ቅዳሜ ሻይ ቡና ለማለት አምስተርዳም ከወዳጆቼ ጋር በነበረኝ ቀጠሮ ላይ እንደአጋጣሚ ተስፋዬም በመሃላችን ተገኝቶ ነበር። የባጥ የቆጡን ስናወራ፣ ስለአዲሱ የተፋስዬ መጽሐፍ አንስቶ የውይይታችንን አቅጣጫ ቀየረው። በመሃሉ ተስፋዬ፣ ከመጽሐፉ ውስጥ አንዳንድ የማልወዳቸው ምዕራፎች ቢኖሩ ትችቶቹን የምቀበል ስለመሆኔ አስረግጦ ጠየቀኝ?።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሲምባ ፍቅር - ትችት (ሐተታ) - ሽፈራው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የመጽሐፉ ርዕስ - የአሲምባ ፍቅር
ደራሲ- ካህሳይ አብር (አማኑኤል)
ትችት (ሐተታ) - ሽፈራው
"ማን ያውራ የነበረ" እንዲሉ "ለቀባሪ አረዱት" እንዳይሆን፤ ለስራ ጉዳይ ወደ ኮሎራዶ (ዴንቨር) በሄድኩበት ጊዜ አማኑኤል ማንጁስ ዴንቨር መኖሩን ሰምቼ ስለነበር ስልክ ደወልኩለት። በአንድ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ተቀጣጥረን ለመ መሪያ ጊዜ ከ30 አመት በኃላ መሆኑ ነው አማኑኤል ጋር ተገንኘን። ለረጅም ጊዜ በዝምታ ከተያየን በኃላ አማኑኤል ሽፈራው አልተቀየርክም አለና እንደገና እቅፎ ሳመኝ። አይ አንተስ ብዙ ተቀይረ ል ማንጁስ አይደለህም? ይህ ውፍረት ይህ ቁመት ከየት መጣ አልኩት። አማኑኤል ብዙ መናገር ሳይፈልግ እንባው ጠብ ጠብ ማለት ሲ ምር እኔም ለምን ታለቅሳለህ? ብዙ መከራ ስቃይ ወጥተን በህይወት ለመገናኘት በመብቃታችን የሚያስደስት ነው። ለአምላካችን ምስጋና የሚገባው ነው ብዬ ለማጽናናት ሞከርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግን እከስሳለሁ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Ehadegen Eksesalehu  by Alemayehu Gelagayeደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ...ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ...ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን...ቢኖሩም...የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው - 'ኢምንቱ' ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዶ/ር ምህረት ደበበ “የተቆለፈበት ቁልፍ”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Yetekolefebet qulfብርሃኑ ሰሙ

ከሁለት ወር በፊት መጋቢት ላይ ነበር “የተቆለፈበት ቁልፍ” የተሰኘው የዶ/ር ምህረት ደበበ ገ/ጻዲቅ ረዥም ልቦለድ መጽሐፍ አንባቢያን እጅ የገባው። መቼቱን በአገር ውስጥና በባህር ማዶ ያደረገው ልቦለድ፤ በ439 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ደራሲው የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስትነት ደረጃ የደረሱት ትምህርታቸውን በአገር ውስጥ በባሕር ማዶ በመከታተል ነው። በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካንና በኢትዮጵያ እየተመላለሱ በሙያቸዉ እያገለገሉ እንደሆነ በመጽሐፋቸው ላይ ተጠቁሟል። ዶ/ር ምህረት፤ ከሐኪምነታቸዉ በተጨማሪ በአስተሳሰብና በአእምሮ ለውጥ ዙሪያ እያስተማሩና ጥናት እየሰሩ እንደሆነ የሚጠቅሰው መረጃው፤ ህብረተሰባዊ ለውጥ ከግለሰቦች የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚጀምር የሚያምኑ መሆናቸውን ይገልፃል። ልቦለድ መጽሐፋቸውም ይሄንኑ የሚያንፀባርቅ ነው። ልቦለዱ በፍቅርና ጥላቻ፣ በደግነትና ክፋት፣ በግልጽነትና መሰሪነት፣ በሀብትና ድህነት፣ በትጋትና ስንፍና፣ በእውቀትና መሃይምነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በጠንካራ የልብ ሰቀላ የአንባቢውን ስሜት ይዞ ከመነሻ እስከ መድረሻ ይዘልቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ