የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፴፱
ሠራበት ትልቅ ፎቅ
እንግድነት መጥቶ፣ “ቤት የእግዜር!” ብንለው
“ገብረ”ን ጨመረና የራሱ አደረገው
አፋችንን ይዘን ገርሞን ስንሳሳቅ
ከቤት አስወጥቶን ሠራበት ትልቅ ፎቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እንግድነት መጥቶ፣ “ቤት የእግዜር!” ብንለው
“ገብረ”ን ጨመረና የራሱ አደረገው
አፋችንን ይዘን ገርሞን ስንሳሳቅ
ከቤት አስወጥቶን ሠራበት ትልቅ ፎቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አልችልም ላወጋው ልናገር ጨርሶ
የዘመኔን ኀዘን የዘመኔን ለቅሶ
ዓይኔም ታዘብኩት ጆሮዬም ገረመኝ
ስንቱን ጉድ አየሁት ስንቱን ጉድ አሰማኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እንዳትቀየመኝ ጥፋተኛ አንተ ነህ
ሁሉ ቦታ ከኔ ማን ብለጠኝ አለህ?
አሁንም እባክህ መብለጥህን ደብቅ
አንተም አትጠላ እኔም አልሳቀቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ብተወኝ ምንአለ?
ዝቅ ካላለብህ ኑሮህ ካልጎደለ
እኔን እንዳመሌ ብተወኝ ምንአለ
አልጨምር አልቀንስ ፍጹም ካንተ ሕይወት
መኖሬ ምንድነው የሆነብህ ፍርሃት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይወረወር ነበር
ሻማ ጉራ ብቻ፤ ቁመታም ቀፈረር
ቆሞ እያለቀሰ ሲያነባ የሚኖር
ክር መኻል ሆና እውስጡ ባትነድ
ይወረወር ነበር እንደ ድንጋይ መንገድ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ከቤትም አንወጣ
አእምሮም ያስባል
ኩላሊት ያጣራል
ልብም ደም ይረጫል
ጨጓራም ይፈጫል
ከሁሉም ከሁሉም - ማን እንደፊንጢጣ
እፎይ ባያሰኘን - ከቤትም አንወጣ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ማረፊያ ያጣች ሞት
ገዳይ በበዛበት በከፋበት ዘመን
ሆኖ ይሰበካል ጭካኔ ቁም ነገር
ያን ጊዜ ከሌለህ ፍቅርና እምነት
ባንተ ትወድቃለች ማረፊያ ያጣች ሞት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 2 / 5





አንዱ ዘፈነብን
አንድ ቅኝት ቃኝተን
አንድ ዜማ አዚመን
ዴሞክራሲ የምትል ግጥምም አጥንተን
ከመሐል ተነስቶ አንዱ ዘፈነብን
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ሰው ሆይ!
ባለብዙ ክብሩ
ባለብዙ ብሩ
ባለብዙ ስፍሩ
ደልቃቃው ቱጃሩ
ሰው ሆይ! ዕድሜ አጭሩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ደም መጦ ደም መጦ
ምከሩት ባካችሁ ያንን ጠብደል ትዃን
መብላቱን እንዲያቆም ከሕመሙ እንዲድን
አለዛ እንዳገኘ ደም መጦ ደም መጦ
እንዳያከረፋን መንገድ ላይ ፈርጦ
ሙሉውን አስነብበኝ ...