የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፵፱
ታዝበው የሚያልፉ
ችላ ብሎ ቢያይህ ዝም ብሎ ቢተውህ
አንተው እንዳትሞኝ ያሞኘኸው መስሎህ
በሆነ ባልሆነው የማይለፈልፉ
ብዙ ሰዎች አሉ ታዝበው የሚያልፉ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5





ችላ ብሎ ቢያይህ ዝም ብሎ ቢተውህ
አንተው እንዳትሞኝ ያሞኘኸው መስሎህ
በሆነ ባልሆነው የማይለፈልፉ
ብዙ ሰዎች አሉ ታዝበው የሚያልፉ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አይጠቅማትም እንጂ ለአገር ከጠቀማት
ምናለበት ነበር ሁሉ ቢሾምላት
ይኸው ስንት ዘመን ሥልጣንን ፍለጋ
አለን ስንፋተግ አለን ስንዋጋ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ኒኬል ቁልፍ ኾኖ ከውጪ ባይጠብቅ
ተዘርፎ ተዘርፎ ይጠፋ ነበር ወርቅ
ዋስትናው ትልቅ ነው አንዱ ላንዱ መኖር
ትልቅ ትንሽ ትተህ በኩልነት አክብር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ወራሪ ደግ ነው እንደምን ይናቃል
ሊገል ሲመጣ እኛን ያስታርቃል።
ተቧጭቀን ተቧጭቀን ብለነው ብለነው
እሱ ሲደርስ ነው አንድ የምንኾነው
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





መለስን አስታወስኩ እስከጭካኔያቸው
አንድ ላይ ነበረ አብረን ምንጠላቸው
ዐቢይ ሲመጡ ደግ ሰው ገራገር
መጨፋጨፍ መጣ በቋንቋና በዘር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ተለፍቶ ተለፍቶ ገንዘብ ሲጠራቀም
ጉሮሮ ይጠባል ይቀንሳል አቅም
ያንጊዜ ቶሎ በል ድንገት እንዳትጠፋ
ሁሉን ቦታ አሲዘህ በደስታ አንቀላፋ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ውስጡ ተከምሮ የሱ የራሱ እድፍ
ሰው በሰው ሲያሳብብ ሰው በሰው ሲለጥፍ
ውስጡን ሳያጠራ ከእውነት ርቆ
ይሔዳል በድንገት ይችን ምድር ለቆ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ትግልና ታጋይ አንዴም ያልተለያት
አለችን አንድ አገር ኢትዮጵያ ምንላት
ጠላቷን ደጋግማ ምንም ብታሸንፍ
ሰላሟን የነሳት አላጣችም ውዝፍ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ሐሜት አቀርሽቶት ፊትህ ሲዝረበረብ
እሱን እዛው ትተህ አስቀምጠህ በገደብ
ምን ያህል እንደሆን ያቦካው ሰው ድምር
ለማወቅ ከፈለክ ጓደኞቹን ቁጠር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አለመተማመን በልባችን ይዘን
እንድንተማመን ሰው አቁመን ማልን
መሃላ ስናፈርስ ሰዉ ዝም ሲለን
በጥፋት ፈራጁን እግዜርን ረሳን
ሙሉውን አስነብበኝ ...