የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፱
አርቀህ ተመልከት
ቅርብ ተመልክቶ ቅርብ ቦታ መስፈር
ይቻላል አውቃለሁ መዋልና ማደር
ሕይወት ግን እስከዚህ አይደለችም አጭር
አርቀህ ተመልከት እንዳይገጥምህ ችግር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





አርቀህ ተመልከት
ቅርብ ተመልክቶ ቅርብ ቦታ መስፈር
ይቻላል አውቃለሁ መዋልና ማደር
ሕይወት ግን እስከዚህ አይደለችም አጭር
አርቀህ ተመልከት እንዳይገጥምህ ችግር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አቀራርበው ካንተ
ውስብስብ በኾነ የሰው ልጅ ተፈጥሮ
ሀሜታ ወቀሳ ሳታበዛ ሮሮ
እንደሰውዬው ልክ ቀንሰህ ደምረህ
አቀራርበው ካንተ ወጥረህ አላልተህ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ማሟላት አትሻ
ስም ይጋነንና ድንገት ከአቅም በልጦ
ያስቀራ አንዳንዴ ዓይን አስፈጥጦ
ከምታውቀው በላይ በሰዎች ስትካብ
ማሟላት አትሻ በማጭበርበር ሂሳብ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ከተማ ልጅነት
የከተማ ገጠር የውልደት አድራሻ
አያስገኝም ቅድሚያ ለዜግነት ድርሻ
እንዲሁም መለያው ከተማ ልጅነት
አይደለም ጨርሶ ተንኮልና ክፋት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ኢትዮጵያዊ
ምነው ድሮ ድሮ በኖርኩና በሞትኩ
ወይም ይሄ ዘመን አልፎ በተፈጠርኩ
እያልኩ ስከፋ ይሄ ዘመን መሮኝ
ይብስ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ተገኘሁኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...




ዝም ብለህ አኑረኝ
በሥራ ቀን ሞቼ ሰው እንዳላስቸግር
ቅዳሜ ግደለኝ እሁድ እንድቀበር
ቅዳሜን ቅዳሜን ሁሌ ካሳለፍከኝ
ምን እጎዳሃለሁ ዝም ብለህ አኑረኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እኔ
እኔ እራሴ እኔ እራሴ መሆኔ
ያጠራጥረኛል እኔነቴ ለኔ
ጠዋት ያልኩትን ቃል ሲመሽ እያፈረስኩ
ሌላ ሰው ነኝ እንጂ ምኑን እራሴን ሆንኩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...




ለምንም አትጠቅም
ከግለሰብ ሙግት፣ በግል አተካራ
ተደፍቀህ ከገባህ እንኳንስ ልትመራ
ከሜዳው ጠርዝ ላይ ይፈሳል ያንተ አቅም
ከቦታው ዞር በል ለምንም አትጠቅም
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





”... በሬ አትሁን” ባለው
ያ መኪና ነጂ ሞተር አንቀሳቃሽ
አንድ ጥቅስ አለችው የጻፋት በብላሽ
”በፍየል ዘመን ላይ በግ አትሁን!” ያለው
ይኼን አባባሉን ምነው በለወጥው
”በአህያ ዘመን ላይ በሬ አትሁን!” ባለው!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ዕድሜ
ይቺን ትንሽ ዕድሜ ይዘን የምንዞራት
እንኳንስ ንትርክ ፀብ ጨምረንባት
እፍ ቢሏት ጭልጥ ትንሽ ናት ደቃቃ
ፍቅር ለማጣጣም እንኳን የማትበቃ
ሙሉውን አስነብበኝ ...