አቶ መለስ ዓለሙ፣ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እና ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ (ከግራ ወደ ቀኝ)

አቶ መለስ ዓለሙ፣ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እና ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ (ከግራ ወደ ቀኝ)

አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ወደ ዋናው ጽ/ቤት ተሹመው ሔዱ
ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በዋናው ፓርቲ ጽ/ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኾነዋል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 24, 2020)፦ አቶ መለስ ዓለሙ የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ተስፋዬ በልጅጌን በምተካት የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኾነው ሲሾሙ፤ አቶ ተስፋዬ በሚኒስትር ማዕረግ ወደ ዋናው የብልጽግና ጽ/ቤት ተዛውረዋል።

ዛሬ ሰኞ ነኀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የወጣው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የሹመት ዜና መሠረት፤ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በሚኒስትር ማዕረግ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ኾነው ተሹመዋል።

ሌላኛው ተሿሚ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ፤ በዛሬው ሹመት የዋናው የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ኾነው እንዲሠሩ ተሹመዋል።

ዶ/ር ቢቂላ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ፤ የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ኾነው ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ