የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ስደት ቁጥር ጨመረ
- ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ፣ ብዛየሁ እና ታምሩ ወደ አገር አይመለሱም!
- ፳፯ የስፖርት ጋዜጠኞች በስደት ይገኛሉ

(ኢትዮኪክ) የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዓመታዊ ስብሰባውን በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በ2008 ሲያካሄድ፤ የማኅበሩ ም/ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ እና ጋዜጠኛ አምሀ መድረኩን ሲመሩት እንደነበር የሚታወስ ነው። ሆኖም ዘንድሮ ሁለቱን ጋዜጠኞች ጨምሮ በማኅበሩ ውስጥ አምና የነበሩ ዘንድሮ በስደት ከማኅበሩ 8 የሚደርሱ የስፖርት ጋዜጠኞች አይኖሩም።
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ አገር ለሥራ አልያም በተለያየ መንገድ ወጥተው ወደ አገር ቤት ሳይመለሱ በስደት የሚኖሩት ቁጥሩ እየጨመረ መጥቷል። በተለይም በሕዝብ ዘንድ በጣም ተደማጭ ከነበሩት ከእነ ፍሰሀ እና አብይ ፍልሰት ጀምሮ፤ ባለፉት ዓመታት በርካታ ታዋቂ እና ተወዳጅ የስፖርት ጋዜጠኞች አገራቸውን ለቀው በስደት በተለያዩ አገራት በተለያየ ሙያ ውስጥ ሕይወትን እንዲገፉ ተገደዋል።
በቅርቡም በጣም ተወደጁ እና ለረጅም ዓመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት እና የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ም/ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ አገሩን ለቆ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አሜሪካ ገብቷል። በሁሴን አብዱልቀኒ ከአገር ለቆ መሄድ ዙሪያ በርካታ አስተያየቶች እየተነገሩ ቢሆንም፤ የሚነገሩት ወሬዎች እውነት ስለመሆናቸው ኢትዮ-ኪክ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጧል።
ከዚህ ሌላ በአትሌቲክ ስፖርት ልዩ ዘገባው ስለ ኢትዮጵያ አትሌቶች በኢንተርናሽናል መገናኛ ብዙኀን በቦታው ተገኝቶ በማስተርጎም እና በመዘገብ የሚታወቀው ቡዛየሁ ካናዳ ገብቶ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ ተሰምቷል። በተጨማሪም በEBC፣ በሬዲዮ ፋና፤ በብሳራት እና ብዙ ሜዲያዎች በመሥራቱ አኔልካ የሚለውን ቅፅል ስም ያተረፊው ታምሩ አለሙ አሜሪካ ገብቶ ወደ አገር ቤት ለጊዜው እንደማይመለስ ተሰምቷል።
ላለፉት ዓመታት ከአገር የተሰደዱ እና በውጭ አገር የሚገኙ የስፖርት ጋዜጠኞች ዝርዝር:-
፩. ፍሰሀ ተገኝ
፪. አብይ ተ/ማርያም
፫. ኢብራሂም ሻፊ
፬. ሁሴን አብዱልቀኒ
፭. ዮናስ ገ/መስቀል
፮. ብዙየሁ ዋጋው
፯. ኢዘዲን ከድር
፰. ታምሩ አለሙ
፱. ሳምሶን ከተማ
፲. ሀና ደምሴ
፲፩. ሂሩት ገ/አምላክ
፲፪. ኃይማኖት (DW-sport)
፲፫. ማርታ በላይ
፲፭. አምሀ ፍሰሀ
፲፮. ዳንኤል ጋሻው
፲፯. ሚሊዮን በላቸው
፲፰. አንዳርጋቸው (ሬዲዮ ፋና)
፲፱. ኤርሚያስ አማረ
፳. ታደሰ ከበደ
፳፩. ዳንኤል (ሀትሪክ ስፖርት)
፳፪. ሱራፌል አሰፋ
፳፫. ደረጄ ተድላ
፳፬. ታምሩ ወልደ ሚካሄል
፳፭. አለሙ መኮንን (EBC)
፳፮. ቤተማሪያም አይሉ
፳፯. አሰግድ ተፈራ
፳፰. ሊባኖስ ዮሀንስ



