በዓለም ሻምፒዮና በ10000 እና በ5 ሺህ በማሸነፍ ለዓለም የመጀመሪያው አትሌት ሆነ

(ተጨማሪ ፎቶግራፎች የታከለበት)

BERLIN: Kenenisa Bekele of Ethiopia celebrates winning the gold medal in the men's 5000 Metres Final during day nine of the 12th IAAF World Athletics Championships at the Olympic Stadium on August 23, 2009 in Berlin, Germany.

Ethiopia Zare (እሁድ ነሐሴ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. August 23, 2009)፦ ኮከቡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊኑ 12ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር አንደኛ በመውጣት ለራሱም ለሀገሩም ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል። በሻምፒዮናው በአስር ሺህ እና በአምስት ሺህ ወርቅ በማግኘት በዓለም ቀዳሚው አትሌት ሆኗል።

 

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድር ታሪክ በ10000 ሜትር እና በ5000 ሜትር አንደኛ በመውጣት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች ያገኘ አትሌት የለም። ኮከቡ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል።

 

አትሌት ቀነኒሳ ውድድሩን የጨረሰው በ13 ደቂቃ ከ17፡09 ሰከንድ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዓሊ አብዶሽ በ13 ደቂቃ ከ19፡11 ሰኮንድ ውድድሩን በስድስተኝነት አጠናቅቋል።

 

በውድድሩ ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ተፎካካሪ ሆኖ የቆየ ቢሆንም ውድድሩን በ5ኛነት አጠናቅቋል። አሜሪካዊው በርናርድ ላጋተ ሁለተኛ፣ የኳታሩ ጄምስ ክዋሊያ ቺኩሩዪ ሦስተኛ፣ የኡጋንዳው ሞሰስ ንዲማ ኪፕሲሮ አራተኛ የወጡ ሲሆን፣ ኤርትራዊው ተክለማሪያም መድኅን ደግሞ ውድድሩን 15ኛ ሆኖ ጨርሷል።

 

ተጨማሪ ፎቶግራፎች

Kenenisa Bekele of Ethiopia (C) celebrates as he crosses the finish line to win ahead of Bernard Lagat of the U.S. (L) and James Kwalia C'Kurui of Quatar (R) in the men's 5,000 metres final during the world athletics championships at the Olympic stadium in Berlin August 23, 2009.
BERLIN - AUGUST 23: Kenenisa Bekele of Ethiopia crosses the line to win the gold medal in the men's 5000 Metres Final during day nine of the 12th IAAF World Athletics Championships at the Olympic Stadium on August 23, 2009 in Berlin, Germany.
BERLIN: (L-R) Bernard Lagat of United States receives the silver medal, Kenenisa Bekele of Ethiopia the gold medal and James Kwalia C'Kurui of Qatar the bronze medal during the medal ceremony for the men's 5000 Metres Final during day nine of the 12th IAAF World Athletics Championships at the Olympic Stadium on August 23, 2009 in Berlin, Germany.
 BERLIN - AUGUST 23: Kenenisa Bekele of Ethiopia celebrates winning the gold medal in the men's 5000 Metres Final during day nine of the 12th IAAF World Athletics Championships at the Olympic Stadium on August 23, 2009 in Berlin, Germany.
 Kenenisa Bekele of Ethopia (L) and campatriot Ali Abdosh hold up their national flag as they celebrate after the men's 5000 metres at the world athletics championships at the Olympic stadium in Berlin August 23, 2009.
 Ethiopia's Kenenisa Bekele bites the gold medal he won in the final of the Men's 5000m during the World Athletics Championships in Berlin on Sunday, Aug. 23, 2009.
 Kenenisa Bekele, Berlin 12th IAAF World Athletics Championships, 10000 m

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ