የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፵፩
አፍህ ብቻ ይረፍ
እንኳንስ ተናግረህ አውጥተህ ካፍህ ቃል
የዛሬ ዘመን ሰው ያሰብከውን ያውቃል
ይህንን በመፍራት በርህን አትቆልፍ
የሰው ስም አታንሳ አፍህ ብቻ ይረፍ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አፍህ ብቻ ይረፍ
እንኳንስ ተናግረህ አውጥተህ ካፍህ ቃል
የዛሬ ዘመን ሰው ያሰብከውን ያውቃል
ይህንን በመፍራት በርህን አትቆልፍ
የሰው ስም አታንሳ አፍህ ብቻ ይረፍ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ባላስከፋ ነበር
መልኩ ተለየ እንጂ በአቀማመጥ በደም
ቆንጆም ቆንጆ አይደለ አስቀያሚም የለም
ቆንጆማ ቢያደርገው አፍንጫና ጥርሱ
ባላስከፋ ነበር በስውር ምላሱ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ሕይወት ይከስራሉ
በክፋት ቢከብሩ በተንኮል ሊያተርፉ
እችላለሁ ብለው በፍፁም አይልፉ
አጋጣሚም ሆኖ ለማግኘት ቢችሉ
ዕድሜ ቅንቡጭ ይላል ሕይወት ይከስራሉ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





አንተ ነህ የምትቀር
ሁልቀን ሌላ ሰው ‘ሚሞት አይምሰልህ
አንድ ቀን ከዛ ቤት አንተም ትጎላለህ
በሞት ተጠፍሮ ያንተ ሁለት እግር
በቀብር ሳትቆም አንተ ነህ የምትቀር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





በአልኮል እንጠበስ!

አውቀንበት ነበር ዋሽቶ በመኖሩ፣
አስቸገሩን እንጂ! ህሊናና እግዜሩ፣
ህሊና አይታሰር እግዜር አይከሰስ፣
እንደ ልማዳችን በአልኮል እንጠበስ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እግርና ጫማ
እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ
በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ
እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው
ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው
በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ
ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የት ይገቡ ይሆን?
ከሀገሬ ነጥቀው የግል ያደረጉኝ
የገዥዎች ንብረት መጫወቻ ዕቃ ነኝ
ብቻ ከተነሳኹ ሠንሠለት ፈትቼ
የት ይገቡ ይሆን እነዚህ ጌቶቼ?
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ህሊና ሲቆሽሽ
ፈልገህ ፈልገህ - ካልተገኘ ተወው
በንጹህ ህሊና - መኖርም ሀብት ነው
ንዋይ ቢትረፈረፍ - ህሊና ቆሽሾ
ማሩ ይመርሀል - ሲገባ እንደ ጌሾ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





አንቆ ይገድለዋል
አጥፊን ከጠፊ ጋር - አቆራኝቶት እግዜር
ሰው ገዳዩን ሳያውቅ - አብሮ ነው የሚኖር
የሩቅ ጠላት አለኝ - እያለ ሲሰጋ
አንቆ ይገድለዋል - የሚወደው ሥጋ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይገጥመዋል ፍዳ
ክብሩን የጠበቀ - የሚያስብ ለራሱ
ብዙ አይለፈልፍም - ቁጥብ ነው ምላሱ
ይህን ያላወቀ - ጠልቆ ያልተረዳ
ያልነካውን ነክቶ - ይገጥመዋል ፍዳ
ሙሉውን አስነብበኝ ...