የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፲፩
ብዙ ተጓዙበት የምርጫውን መንገድ
መኖሩን ረስተው አለምርጫ መውረድ
የተገናኙለት ምርጫና ፍጥጫ
አወይ መከራዋ የሹም መቀመጫ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ብዙ ተጓዙበት የምርጫውን መንገድ
መኖሩን ረስተው አለምርጫ መውረድ
የተገናኙለት ምርጫና ፍጥጫ
አወይ መከራዋ የሹም መቀመጫ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ለካስ ትክክል ነው የደም ስር ነው ገንዘብ
አንድ ጉድ አየሁኝ ባሳለፍነው ሮብ
ማሙዬ መንገድ ላይ ሳንቲም ተመልክቶ
ዱብ አለ ሊያነሳ ማሰሪያውን ፈቶ
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ማነው የመከረው ይህ ሁሉ ሙሽራ
ዝም ብሎ ያገባው ትዳርን ሳይፈራ
ሁሉንም ይወቁት በሉ ንገሯቸው
ሲኦልና ገነት ትዳር ማህል ናቸው
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ያላልኩትን አልኩኝ ያልኩትን አላልኩም
ሞት ይመጣል እንጂ በፍጹም አልልም
ብለሃል ያለኝን እንግዲህ ጥሩልኝ
አላልኩም አልልም ብለሃል ይበለኝ
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ሚዛናዊ ሆነህ በሰላም ብትጓዝ
ጨዋነት ራሱ አለው ትንሽ መዘዝ
ይህ ሁሉ ደግነት አይደለም ለጤና
ሊሉህ ይችላሉ ይጠረጥሩና
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





እባብ መሃላ አርጎ ደግ ሰው እንዳይነድፍ
አንዱ ተኝቶ አየ አሸንፎት እንቅልፍ
ይሄ አይታወቅም ሲነሳ መዘዙ
በማለት አቅምሶት አለፈ ከመርዙ
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የሰው ልጅ ተፈጥሮ መልኩማ መች ታጣ
ድብቅ ባህሪው ነው ልዩነት ያመጣ
መልኩም አይለወጥ ባህሪውም ይኑር
ውሃ ልኩ እሱ ነው ሚዛኑ የመኖር
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ያገሬ ሰው ሰልጥኗል
ከልቡ ተናግሮህ ቀልዴን ነው ይላል
ደግሞ እኮ የጠረጠረህ
እሱን መሆንህን ሊያውቅልህ
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





አታካቿን ሕይወት
መራራዋን ስደት
በጨው አጣፍጫት
ቅባት ጨምሬባት
ዕድሜዬን ራሴ
ለራሴ በላኋት
ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ጋዜጠኛ: ክቡር አቶ መለስ ሰዎች አስከትለው
ባቡሩን መረቁ በስፍራው ተገኝተው
አዝማሪ: መለስ አልሞቱም ወይ? እንዴት ነው ነገሩ
ሲጠሩ ሰማሁኝ ሲመረቅ ባቡሩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...