የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወሰነ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት
የፌዴራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳለፈ
ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 7, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴራል መግንሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባና ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የቀረበለትን ሐሳብ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ሥራ አስፈጻሚ ታግዶ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ አስፈጻሚውን የመምራት ኃላፊነት ይኖረዋል። ከዚህም ሌላ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ አስፈጻሚ ምርጫ የማካሔድ ኃላፊነት የሚሰጠው ነው። (ኢዛ)



