የእግዚአብሔር ምስክሮች እንሁን (ጸደንያ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክ በቫንኩቨር)

በስመ አብ በወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!!

 

ከቫንኮቨር ፀደንያ ቅድስት ማሪያም  ቤተክርስትያን  የተሰጠ የአቋም  መግለጫ በሕጋዊውና በብፁእ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያስተላለፈዉን የአቋም  መግለጫ ስለመደገፍ።

 

ለአምላካቸዉ  ለእግዚአብሄር አምላክነት በግልፅ ስለመሰከሩና  ስለተጋደሉ አባቶቻችን በቅዱሳን  መጻህፍት እንደተፃፈው   በብሉይ ኪዳን   ነቢያት አባቶቻችን ፣ በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያት አባቶቻችን ፣ ባደረጉት ተጋድሎዎች ተጠብቆ የኖረዉን ስርዓት እኛም  በዚህ ዘመን የምንገኝ በክርስቶስ ደም የቆመችዉን የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንን ዶግማና ቀኖናዋን  ሳይፋረስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ብሎም ለትውልድ የማስተላልፈ  ክርስቲያናዊ አደራ አለብን።

 

(ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

"የህወሓት/ኢህአዴግን አሸባሪ አገዛዝ በጋራ እንታገል" ሸንጎ

ከ”የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ” የተሰጠ መግለጫ

የካቲት 2፣ 2005 (Feb 9, 2013)

ባለፉት ጥቂት ቀናት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በቁጥጥሩ ሥር የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አገልግሎቶችን በመጠቀም፣ በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎችን የሚወነጅል ሠፊ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥያቄዎቻችን በጆሮ ዳባ ልበስ ሊታለፉ አይገባም!

ጥያቄዎቻችን በጆሮ ዳባ ልበስ ሊታለፉ አይገባም፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ ተገደው እንዲሰሙ የማድረግ ህዝባዊ ትግል ይቀጥላል!!

ከ33ቱ የፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች ባቀረብነው ጥያቄ ዙሪያ በቀጣይ የጋራ አቋም ላይ የተሰጠ መግለጫ

1. መግቢያ

በአዳማ ከተማ በ2005 ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለማወያየት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰበሰበን ወቅት ከተሣታፊ 66 ፓርቲዎች 41ዱ ከጊዜ ሠሌዳው በፊት የውድድር ሜዳውን መስተካከል በሚመለከቱ አበይት የምርጫ ጉዳዮች ልንወያይ ይገባል ከሚለው ኃሣብ በመነሣት እና በጉዳዩ ለመግፋት ፔቲሽን ፈረምን፡፡ በመቀጠልም በ29/02/05 ዓ.ም 18 ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ /ኢብምቦ/፣ 13 ጥያቄዎችን ደግሞ በ08/04/05 ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት አቅርበን ከቦርዱ ጥያቄአችሁ “ውሃ አያነሳም” በሚል ሙሉ በሙሉ ውድቅ መደረጉ በ10/04/05 ዓ.ም በቃል ሲገለጽልን፤ ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት፣ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽ/ቤት መልስ እየጠበቅን መሆኑን ገልጸን መልስ መጠባበቃችንን ቀጠልን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ሕገ-መንግሥቱን የሚፃረርና የሻረ ነው!

ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ፔቲሽን ተፈራርመው

ለምርጫ ቦርድ ጥያቄዎቻቸውን ከአቀረቡ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት በሕገ-መንግሥቱ የሰፈሩትን ለሕዝብ የተሰጡ መብቶች እንደፈለገውና እንዳመቸው በማንአለብኝነት ሲጥስና ሲደፈጥጠው ለመኖሩ ያለፉት ተግባራቱና በዚህ ሹመት ያየነው ድርጊቱ የሚመስክሩት ሐቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ