70 Ethiopians died on boat accident

ከሟቾቹ ውስጥ ስልሳ ያህሉ ትግራይ ክልል ከሚገኘው አፅቢ ወንበርታ ከሚባል ወረዳ የተነሱ መሆናቸው ታውቋል

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፰ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. April 16, 2019)፦ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት መጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ ዐረቢያና የመን በመጓዝ ላይ የነበሩ ሰባ የሚኾኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በባሕር ላይ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸውን እንዳጡ ተነገረ።

ከሟቾቹ ውስጥ ስልሳ ያህሉ ትግራይ ክልል ከሚገኘው አፅቢ ወንበርታ ከሚባል ወረዳ የተነሱ መሆናቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የገለጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የአርባዎቹን ወጣቶች ሞት ማረጋገጡ ታውቋል። በቁጥር ከታወቁትና ከትግራይ ክልል ከተነሱት ከስልሳዎቹ ሟቾች በተጨማሪ የሞቱት ወጣቶች ኢትዮጵያውያኖች መሆናቸው ቢታወቅም፤ ከየትኛው የአገሪቱ ክልል እንደተነሱና ትክክለኛ ቁጥራቸው አልታወቀም።

አደጋው ከደረሰባቸውና መሞታቸው ከተረጋገጡት ለአርባዎቹ ወጣቶች ቤተሰቦች ሚያዝያ 6 እና ትናንት ሰኞ ሚያዝያ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. መርዶ እንደተነገራቸው የትግራይ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባወጣው የኀዘን መግለጫ አረጋግጧል። እንዲህ ዐይነቱ የጀልባ አደጋ በተለይ በኢትዮጵያውያውያንና በኤርትራ ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ሲደርስ ቢቆይም፤ መፍትሔ ያላገኘ ጉዳይ እንደኾነ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዛሬ የዝግጅት ክፍል በወገን ላይ በደረሰው አሳዛኝ ሞት ኀዘኑን ይገልጻል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ