Elias Melka

አርቲስት ኤልያስ መልካ

ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 5, 2019):- በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኹነኛ ስም ያለውና የብዙ ወጣትና አንጋፋ ድምፃውያንን ሙዚቃ በማቀነባበር የሚታወቀው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ኤልያስ የስኳር፣ የኩላሊትና የልብ ሕመም ገጥሞት ሕክምናውን ሲከታተል ነበር።

ኤልያስ ያረፈው በመኖሪያ ቤቱ ለሊት ላይ መሆኑ ታውቋል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ኤልያስ መልካ ከ30 በላይ የሚሆኑ አልበሞችን አቀናብሯል።

በኤልያስ መልካ አቀነባባሪነት ጆሮ ግቡ የሆኑ ሙዚቃዎቻቸውን ለሕዝብ ካደረሱ ታዋቂ ሙዚቀኞች መካከል ቴድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ አለማየሁ እሸቴ፣ መሐሙድ አህመድ ይገኙበታል።

ከወጣት ድምፃውያን ደግሞ እንደ ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ትግሥት በቀለ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ሌሎችም በርካታ አርቲስቶች የአቀናባሪውን የጥበብ ሥራዎች፣ እጅግ ጥዑም የሚባሉ ሙቃዎቻቸውን ለሕዝብ አድርሰዋል። (ኢዛ)

ከአዘጋጁ፣

የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ መልካም አሻራውን ባሳረፈው አርቲስት ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል። ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ