ደራሲ ሰለሞን ሐለፎም አዲስ መጽሐፍ አስመረቀ

Svensk grammatik på amhariska för nybörjare

ኢዛ (ሐሙስ ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. May 16, 2019):- የስዊድንኛ ሰዋስው በአማርኛ ለጀማሪዎች (Svensk grammatik på amhariska för nybörjare) በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ ደራሲ ሰለሞን ሐለፎም ሜይ 5 ቀን 2019 እ.ኤ.አ. (ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም) በስቶክሆልም አስመረቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የጋጥ ወጦች ድርጊት ትግላችንን አይገታውም” የአዲስ አበባ ባላአደራ ምክር ቤት

ባልደራስ

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፱ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. April 17, 2019)፦ በአክቲቪስትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ቅዳሜ ሚያዚያ 5 ቀን 2011 ከሕዝብ ጋር ሊያደርግ የነበረውን ስብሰባ በደረሰበት ጫና ለመሰረዝ መገደዱ ታወቀ። ይኼንኑ በተመለከተ ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ”የጋጥ ወጦች ድርጊት ትግላችንን እንድናጠናክር ያደርገናል" በሚል ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ክስ ተመሰረተባቸው

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ

ኢዛ (ረቡዕ ሚያዝያ ፱ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. April 17, 2019)፦ ከዳሽን ቢራ አክሲዮን ማሕበርና ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች ጋር ተያይዞ በምዝበራ/ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ክስ ተመሰረተባቸው። ተከሳሾቹ ጠበቆቻችን የክርክሩን ሒደት ከአዲስ አበባ ኾነው በፕላዝማ ይከታትሉልን ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ችሎቱ ውድቅ አደረገው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሰባ በላይ ኢትዮጵያውያን በጀልባ መገልበጥ ሕይወታቸውን አጡ

70 Ethiopians died on boat accident

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፰ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. April 16, 2019)፦ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት መጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ ዐረቢያና የመን በመጓዝ ላይ የነበሩ ሰባ የሚኾኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በባሕር ላይ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸውን እንዳጡ ተነገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእኔ ሽበት የግጥም መድብል ተመረቀ

የእኔ ሽበት

(ኢዛ) በገጣሚ በማትያስ ከተማ (ወለላዬ) ተደርሶ ለንባብ የበቃው “የእኔ ሽበት” የግጥም መድብል መጽሐፍ ቅዳሜ ኦክቶበር 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ተመረቀ። ምርቃቱ የተደረገው ስቶክሆልም፣ ቮርበሪ ሴንትሩም አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የስብሰባ አዳራሽ ሲሆን፤ በዝግጅቱ ላይ የደራሲው ቤተሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦሮምኛ በግዕዝ እንዲጻፍ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጠየቁ

ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያውይና ብቻ ሳይሆን የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነው፣ ብቃት ያለው፣ የግዕዝ ፊደል እያለ፣ የላቲን ፊደልን ለኦሮምኛ መጠቀም ትክክል እንዳልነበረ ገልጸው፤ ላቲን በአፋን ኦሮሞ እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ እንዳሳደረበትና ቋንቋውን በተቀረው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ እንዳያድግ መሰናክል እንደሆነ በመግለጽ፤ አፋን ኦሮሞ በግዕዝ መጻፍ እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ደጉ አንዳርጋቸው ኦሮሞኛ በአማራ ክልል በግዕዝ ፊደል በትምህርት ቤቶች እንዲጀመር ተጠየቁ

Degu Andargachew

ምሁራን/አክቲቪስቶች ኦሮሞኛ በአማራ ክልል በግዕዝ ፊደል እንደ ትምህርት እንዲሰጥ ጠየቁ

“በባዕዳን ፊደል የሚጽፉ አፍሪካውያን፣ በአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ሲገዙ የነበሩና ራሳቸው የፈለሰፏቸው የፊደላት አማራጭ ያልነበራቸው ሕዝቦች ናቸው። እኛ በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ደምና አጥንት ነፃነታችን ተከብሮልን የኖርንና አኩሪ ቅርስ የሆነ የራሳችን ፊደል ያለን ሕዝቦች፤ ቅኝ እንደተገዙትና እንደተዋረዱት ያልታደሉ ሰዎች ልንሆን አይገባም።” ሲሉ ታዋቂ ምሁራን እና አክቲቪስቶች፣ አሮምኛ በአማራ ክልል በግዕዝ ፊደል እንዲሰጥ የሚጠይቅ ጥናታዊ ሰነድ አዘጋጅተው ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስገቡ። ደብዳቤውን ከአባሪ ሰነዶች ጋር በዚሀ ጽሑፍ አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈረዳባቸው

Eshetu Alemu

ዘሄግ (ታኅሣሥ ፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም. / 15 Dec. 2017) ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ ዓለሙ አቃቤ ሕግ በቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ ዕድሜ ልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሰባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ እንዲህ ዐይነት ፍርድ በሆላንድ አገር ሲሰጥ የመጀመሪያው መሆኑን አቃቤ ሕግ ተናግረዋል። በአገሪቱ ሕግ የዕድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ባለሀብቱ ሼህ መሐመድ ሑሴን አል-አሙዲን በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ

Sheikh Mohammed Hussein Al-Amoudi

ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም. November 5, 2017)፦ በኢትዮጵያ ከኢሕአዴግ ኢንዳውመንት ድርጅቶች በመቀጠል የአገሪቱን ሀብት በሁለተኛ ደረጃነት ይቆጣጠሩታል ተብሎ የሚነገርላቸው ባለሀብቱ ሼህ መሐመድ ሑሴን አል-አሙዲ በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!